ዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት

የፍራንኮ-ኢትዮጵያ የላሊበላ ቅርስ ጥገና፣ እንክብካቤና እሴት መጨመር ፕሮግራም

 
 

ስለ ፕሮጀክቱ

ዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት 

ይህ ፕሮጀክት የላሊበላን ቅርስ የመጠገን ፣ የመንከባከብ እና ቅርሱ ላይ እሴት መጨመር በሚል መርህ የፍራንኮ-ኢትዮጵያ ትብብር ፕሮግራም አካል ነው ፡፡ ይህ ፕሮጀክት በፈረንሣይ የልማት ኤጀንሲ (AFD) የገንዘብ ድጋፍ፣የፈረንሣይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል (CFEE) እና በፈረንሣይ ብሔራዊ ሳይንሳዊ ምርምር ማዕከል (CNRS) ተግባራዊ የሚሆን ነው፡፡ በቅርሱ ላይ የሚደረግን አስቸኳይ ጥገና ጨምሮ ለኢትዮጵያን ተማሪዎች እና ለሙያተኞች የሥልጠና መርሃግብርን ያካተተ ስራ ሲሆን በቅርስ አያያዝ ላይ የአቅም ግንባታ ስራና የቅርስ አስተዳደር ስልጠናንም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

 
 

የድረ-ገጹ አጠቃቀም

የዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት ድረ-ገጽ በሶስት ቋንቋዎች (አማርኛ፣ ፈረንሳይኛና እንግሊዘኛ) ለበርካታ አንባቢዎች ተደራሽ እንዲሆንና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል ተደርጎ የተዘጋጀና ሳይንሳዊ፣ መስተጋብራዊና አዝናኝ እንዲሆን የታለመ ነው። ድረ-ገጹ ስለ ፕሮጀክቱ ከማሳወቁም በላይ የላሊበላን ከተማ በበቂ ለመረዳት አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ማለትም ታሪኳን፣ ነዋሪዎቿን፣ የከተማ አደረጃጀቷን፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ተግባራትን፣ ሳይንሳዊ ስራዎችን፣ ወዘተ ያቀርባል። ድረ-ገጹ በማህበራዊ ሳይንስ የጥናት ዘዴ የተደገፈ የጽሑፍና የኦዲዮቪዥዋል ግብአቶችን ያካትታል።

ይህ ኘሮጀክት ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተሰራ ሲሆን ድረ-ገጹ የሚያሳየውም ይህን ሂደት ነው። እያንዳንዱ የፕሮጀክቱ እድገትና የስራ ደረጃዎች፡- የጥገና ስራዎች፣ የምርምር፣ የአቅም ግንባታና የእሴት መጨመር ስራዎች፣ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ በሰነድነት ይቀመጣሉ፣ ይታተማሉ። ይህ ፕሮጀክት እንደ ድረ-ገጹ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይሆናል። ተመራማሪዎች፣ የዩኒቨርስቲና ሌሎች ተማሪዎች፣ እንዲሁም መምህራን ለሳይንሳዊ ምርምር ስራዎቻቸው፣ ለተለየ ጉዳይ ጥናቶቻቸው ወይም የእውቀት ማግኛ ጉጉታቸውን ለማሟላት አስፈላጊውን ግብአቶች ያገኛሉ።