የጥናት ዘዴ

ለዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት

የጥናትና ምርምር ስራው ለረጅም ጊዜ በጥምር-ሙያተኞች (ኢትዮጵያዊያንና አለም-አቀፍ ቡድን) አማካኝነት ሲካሄድ በመቆየቱ፤ ለፕሮጀክቱ ራሱን የቻለ የጥናት ዘዴ አበርክቷል፡፡ በዚህም መሰረት የመስክ ቅኝትን፣ መረጃ መተንተን፣ እንዲሁም መረጃ ማሳወቅንና መከታተልን ያካትታል፡፡  ጥምር-ሙያተኞቹ ከተለያዩ የሞያ ዘርፍ የተውጣጡ ባለሞያዎች ሲሆኑ፤ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የስነ ቁፋሮ ባለሙያዎች፣ የአለት (ድንጋይ ጥገና) ጠራቢ እና የስነ-ምድር ባለሙያዎችን በአንድነት በመያዝ የላሊበላ ከተማን ጥልቅነት፣ ስብጥርነት እና ሂደታዊ ለውጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ወደ ስራ የገቡት፡፡ ፕሮጀክቱ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው በብሔራዊ ሳይንሳዊ ምርምር ማዕከልና የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የሚመራና፣ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በላሊበላ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ሲያደርግ ከቆየው ከባህላዊ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን በጋራ ሲሰራ ቆይቷል።

 

የ2013 አርኪዮሎጅ ቁፈራ በቀይት ተራራ

 



የአስቸኳይ ጊዜ ቅርስ ጥገና ስራዎች

ለፕሮጀችቱ ወርክሾፕ መድረክ ማዘጋጀት

የመንከባከብ ስራ ከመጀመሩ በፊት፣ 24 የአስቸኳይ ጊዜ ቅርስ ጥገና ስራዎች ተከናውነዋል። እነዚህ ስራዎች፣ በአንትዋን ጋሪክ፣ የድንጋይ አናፂ ባለሙያና የዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት የአስቸኳይ ጊዜ ቅርስ ጥገና ስራዎች መርሃ ግብር ኃላፊ የተሰሩ ሲሆን፣ ዓላማውም ስፍራውን ለተሳላሚዎችም ሆነ ለህዝበ-ክርስቲያኑ ምቹ ሆኖ እንዲያገለግል ማስቻል ነው።

ስልጠናው፣ የ20 እደ ጥበብ ባለሙያዎች የመስክ ስልጠናን ጨምሮ፣ የብየዳ፣ የድንጋይ አጠራረብ፣ የእንጨት ቅርፃቅርፅ አሰራር፣ የካርታ ንባብና ንድፍ ክህሎቶች ስልጠናን በማካተት የአገር በቀል ዕውቀቶች የሚጎለብቱበትን መንገድ ያመቻቻል።

 
 



የአቅም ግንባታ

በስልጠናው ላይ የቅርስ ጥበቃውን፣ የቅርስ እንክብካቤ እና የቅርስ ደረጃን አጠባበቅ በማካተት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎቸና ባለሙያዎች ፕሮጀክቱ በቅርስ ጥናትና አስተዳደር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በሌሎቸ የቅርስ ቦታዎችም ተግባራዊ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ቀዳሚ ተግባሩ  ኢትዮጵያውያን ከባህል፤ ከቅርስ እና ቱሪዝም አንጻር ቅድሚያ የሚሰጡትን ጉዳይ በመደገፍ ማህበራዊ ተሳትፎን አካታች እንዲሆን ያደርጋል፡፡

 
 
 



አሳታፊነት

የላሊበላ ማህበረሰብ ለፕሮጀክቱ መልካም ጅማሮ እንዲሁም በጎ ፍጻሜ ሊኖረው የሚያስችለው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊነት ሲታካልበት ነው፡፡ ይህም ሲባል ፕሮጀክቱ የታሰብለትን ግብ እንዲመታ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ፣የልምድ ልውውጥን ማካሄድና በትምህርት የታገዘ ስረአት በመፍጠር ተመልካችነትን ወይም ጠባቂነትን በማቆም ዘላቂ ተግባራትን ማከናወን  ይቻላል ተብሎ ይታመናል።