የላሊበላ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ

ላሊበላ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ በሰሜን ኢትዮጵያ ተራራማ ቦታዎች መሃል፣ ከአዲስ አበባ 700 ኪ.ሜ ርቀት ላይ፣ ከአሸተን ተራራ በስተግርጌ፣ በአቡነ ዮሴፍ ኮረብታ (4 200 ሜትር ከፍታ) እና በተከዜ ኮረብታ (1 800 ሜትር ከፍታ) መካከል በመካከለኛ ስፍራ ላይ ትገኛለች።

በላሊበላ ከተማ 60,000 የሚሆኑ ነዋሪዎች ይኖራሉ። በ1980ዎቹ ላሊበላ ወደ 4,000 የሚሆኑ ነዋሪዎች ያሏት መንደር ነበረች። የከተማዋ ኢኮኖሚ በቱሪዝምና በግብርና ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። የቅርስ ሀብትና የቱሪስት ልማትና እሴት መጨመር ስራ ለፈጣን የከተማ ልማት አስተዋፅዖ ያበረከቱ ሲሆን የላሊበላን ገፅታዎችም በእጅጉ ቀይረዋል። 

ባለፉት አስርት ዓመታት፣ ከተማዋ የትራንስፖርት፣ የጤና፣ የትምህርትና የቱሪስት መሠረተ ልማቶች ተዘርግቶላታል። በ2000ዎቹና በ2010ዎቹ ዓመታት፣ ከቱሪስት ልማት ጋር በተያያዘ፣ የላሊበላ ከተማ አደረጃጀት ተቀይሯል። ከተማዋ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት ወደ 50,000 የሚጠጉ አለምአቀፍ ቱሪስቶችን አስተናግዳለች። አሁን ያለው ሁኔታ በቱሪስት ገቢ ላይ የተመሰረተውን ኢኮኖሚውንና ማህበረሰቡን ክፉኛ ጎድቷል።

የበለጠ ለማየት ምስሉን ይጫኑት - Google Earth

ላሊበላን በካርታ

ቅርሱ በጊዜ ሂደት ያመጣው ለውጥ

የላሊበላ መልካምድር



የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት

ላሊበላ ከመካከለኛው ዘመን አንስቶ የረጅም ጊዜ የለውጥ ሂደት ውጤት ነው።

በተራራማው የሰሜን ኢትዮጵያ እምብርት ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ የአስራአንዱ ውቅር አብያተክርስቲያናት መገኛ ነች፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱን በማሳነፅም ሆነ በማነጹ ቅዱስ ንጉስ ላሊበላ ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ትውፊት እንደተጻፈው፣ ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀመሮ ንጉስ ላሊበላ የክርስትና ስርወ መንግስት ውስጥ የበላይ መሪ ሆነው አገልግለዋል።  ከለተ ዕረፍታቸው በኋላ   ቅዱስ ስፍራው (የቦታው ስም)  እንደተቀየረና ስሙም ላሊበላ እንደተባለ ታሪክ ያስርዳል፡፡ ይህ ሥፍራ ለረጅም ጊዜ ልዩ ልዩ ክስተቶችን  ያስተናገደና የዚህም ውጤት ነው። ይህም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን በፊትና ከዛ በኃላ ያላቋረጠ ክዋኔ መሆኑን አመላካች ግኝቶችን በምርምር ማየት ተችሏል። ይህን ለመረዳት ከብዙ ዘመን ክራሞትና (የቆይታ) ጥናት በመነሳት የዛን ዘመን ክስተት አዲስ የአርኪዮሎጂ ስርዐትን በመዘርጋት  የቀደመውን በመከለስ የተከናወነ ሲሆን በተደጋጋሚ በሚከሰተው የአየር ጠባይ ለውጥ የላይኛው የአለቱ ክፍል በዝናብ መሸርሸር ፣ ለጸሃይና ንፋስ መጋለጥ ቀድሞ የነበረውን ውብ ይዘት እንዲያጣ ወይም እንዲቀይር ያደረገው መሆኑን መገንዘብና ማወቅ ተችሎል።

ላሊበላ ዳግማዊ ኢየሩሳሌምን እንድትሆን ተብሎ በኢትዮጲያዊያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ ቅዱስ ስፍራ ሲሆን የቅዱስ ስፍራዋን (እየሩሳሌምን) ስያሜ ተጋርቷል፡፡ እንደ ሃይማኖታዊ ትውፊቱ አገላለጽ፤ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ ራሱ የተቀበረው በጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን፣ የቅዱስ ስፍራው ጎልጎታ እና በኋላም ቅዱስ የሆነው ንጉስ ላሊበላ የቀብር ስፍራ በአንድ ላይ መገኘት ላሊበላን ታላቅ የመንፈሳዊ ስፍራ ማዕከል አድርጓታል፡፡ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለኦርቶዶክሳውያን ዛሬም ድረስ በአፍሪካ ጎልተው ከሚታዩ ቅዱሳን ስፍራዎች መካከለ አንዱ ሲሆኑ አብያተ ክርስቲያናቱ በየአመቱ በታህሳስ ወር መጨረሻ ለሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስና የቅዱስ ላሊበላን ልደት ለማክበር የሚመጡን በመቶ ሺዎች  የሚቆጠሩ ምዕመናን የሚያስተናግድ ታላቅ ስፍራ አድርጓታል፡፡

ቤተ አማኑኢል

የስፍራው እይታዎች

የስፍራው እይታዎች© ላሊበላ፣ ኢትዮጵያ፣ ፕላንና የመሬት አቀማመጥ ካርታ አዲስ አበባ፣ CFEE፣ 2011

አብያተ ክርስቲያናት



የሚኖርበት ቅርስ

ህጻናት ከበሮ እየመቱ በበአል ውርርስ

በአመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳላሚ ወደ ቦታው የሚጎርፍ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ነዋሪ ህዝበክርስቲያኑ እለት ተእለት የሚከወንን ሃይማኖታዊ ክዋኔን በአብያተክርስቴያናቱ ያለማቆረጥ ይፈጽማል። በዚህ ቅዱስ ስፍራ ከ1000 በላይ በሚሆኑ ካህናትና ዲያቆናት ሃይማኖታዊ አገልግሎትን ሳይታክቱ ይሰጡበታል፡፡ አብያተክርስቲያኑ የላሊበላን  እና የአካባቢው ምእመናን ብቻ ሳይሆን ለገና በዐል ለሰኔ ሚካኤል ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ምዕመናንና ለማንኛውም አይነት ሃይማኖታዊ ሥርዓት እና ክብረ በዓላትን ያለማቋረጥ እሚያስተናግዱ  ናቸው፡ ከዚህ ጎን ለጎን ይህ ቅዱስ ስፍራ በውስጡ ከ60000 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ይዞል፣ ይህን ሁሉ ተግባራት የሚያስተናገደው የላሊበላ ከተማ፣ከመሰረተ-ልማት አንጻር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል ስራ አልተሰራም። በቀላሉ የተቆራረጠውን የከተማውን ክፍል የሚያገናኝ መንገድ፣ ለኗሪውም ሆነ ለጎብኝ የሚሆን መጸዳጃ፣ የመንገድ ላይ መብራት፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በውል ያልተደራጀ ከመሆኑ በላይ የከተማው ፕላን ለዚህ ቦታ ተመጣጣኝ አለመሆኑ እጅግ ያሳስባል። በአብዛኛው አብያተክርስቲያናቱ ቅጥር ሰፍረው ይኖሩ የነበሩ የአካባቢው ኗሪዎች  ቀስ በቀስ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች አማካኝነት ከክልላቸውና ከቦታው ርቀው እንዲሰፍሩ የተደርገ ሲሆን እነዚህ የማሀበረሰብ ክፍሎች ያልተደላደለ አሰፋፈርና ያሉበት ቦታ ከሚውዱት ቅርስ ጋር እሚያገናኝ ትራንስፖርት አለመኖር ኑሯቸውን አክብዶታል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ የተለቀቀ የቅርስ ክልል ለተሳላሚዎችም ሆነ ለሀዝበ ከርስቲያኑ ምቹ ሆኖ እንዲያገለግል ክልሉን የማስተካከልና የማስዋብ ስራ ይጠበቃል።

 

የዕለት ተለት ምዕመናን

ተሳላሚዎች



አደጋ የተጋረጠበት ሕያው ቅርስ

ይህ ሕያው ቅርስና የሃይማኖት ማዕከል በተባበሩት መንግሰታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) በአለም ቅርስነት እ.ኤ.አ. በ1978 የተመዘገበ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ለአደጋ ተጋልጦ ቆይቷል፡፡ ለዚህም በዋነኛነት የዝናብና ጸሃይ መፈራረቅ አለቱ በከፍተኛ ደረጃ እንዲሸረሽር እና ለአደጋ ተጋላጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ አብያተክርስትያናቱን ከአደጋ ለማዳን የተለያዩ ጥገናዎች እና እድሳት ሲደረግላቸው እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ፡፡ ከተደረጉት የተለያዩ የጥገና ሙከራዎችና ጥናት በመነሳት የአለት ጥገና ሂደትን በመምረጥ የአለት ጥገና ሊደረግ የሚገባ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል፡፡ እ.አ.አ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ቅርሶቹን ከዝናብ ለመከላከል ልዩ ልዩ የመጠለያ ስራ ሲሰራላቸው መኖሩ ይታወቃል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የቆርቆሮው ጣራ ተነስቶ በዘመናዊ መጠለያ እንዲቀየርም ተደርጓል፡፡ መጠለያው የተሻለ አማራጭ እንዲሆን በሚል የመፍትሄ ሃሳብ ቀርቦ ቢዘጋጅም ለረጅም ጊዜ መቆየት እንዲችል ወይም በቅርሱ ላይ አንዳች አደጋ እንዳያደርስ ተብሎ የተከወነ ተግባር ግን አልነበረም፡፡ 

የላሊበላን አብያተክርስቲያናት መጠበቅ ለእምነቱ ተከታዮች የቀን ከቀን ሃይማኖታዊ ተግባራትን ለመፈጸም ፣ የሃይማኖታዊ ጉዞዎችን ለማስኬድ ፣ የጎብኝዎችን ጉዞ ከማሳለጡም በላይ የቤተክርስቲያናቱ መታደስ የቦታውን የቀደመ ክብሩን መልሶ እንዲጎናፀፍ ያስችለዋል፡፡ ይህንን ለማሳካትም በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የቤተክርስቲያኑ የበላይ ሃላፊዎችና የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ቤተ ማርያም

የቅርሱ ለአደጋ መጋለጥ በምስል

ተያያዥ