የላሊበላ ፕሮጀክት

እ.አ.አ. በመጋቢት 2019 በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መንግስት መካከል የተፈረመው የጋራ  ስምምነት የላሊበላን አብያተ ክርስቲያናትን መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ ቅርሱን ማልማትና ማሳደግን ማዕከል ያደረገ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት የባሀል ጥበቃና ቅርስ ስምምነት ነው። የገንዘብ እገዛ የሚደረግለት በፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ቢሮ (MEAE)፣ በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) እና በብሔራዊ የሳይንስ ጥናት ማዕከል (CNRS) መሆኑ ይታወቃል፡፡  የላሊበላን-ማስቀጠል ፕሮጀክት በበላይነት የሚመራው በአዲስ አበባ የሚገኘው የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከልና (CFEE) በፈርንሳይ ሀገር የሚገኝው ብሄራዊ ምርምር ማዕከል በጋራ በመሆን ነው፡ ፡ ይህ የላሊበላን-ማስቀጠል ፕሮጀክት አጠቃላይ የላሊበላ ፕሮግራም (መርሃ ግብር) አካል ሲሆን በውስጡ የሚያካትታቸውም የዲጂታል አውደ-ርዕይ፤ የአርኪዮቪዥን ላብራቶሪ (CNRS)፣ ዓለም አቀፍ የቅርስ ጥገና ስትራቴጂ እና የዘላቂ ቅርስ ጥበቃና ቅድመ ጥገና ስራን ለማከናወን እንዲያስችል ተደርጎ የተቀርጸ ነው።

 

ላሊበላን በዘላቂነት የማስቀጠል ፕሮጀክት

    • ቅድሚያ የሚሰጣቸውና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኙ በ22 የተመረጡ ቦታዎች ላይ የጥገና ስራ መስራት፣

    • በቅርስ ጥበቃ፣ጥገና እና ቅርስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣

    • የስፍራውን ታሪክ እና መስህብነት ከፍ ማድረግ፣

    • የዲጂታል መረጃ ማዕከል ማቋቋም፣

    • በጉዳት ላይ የሚገኙ የስእልና ምስል ጥገና ማካሄድ፣

    • የኤሌክትሪክና ድምጽ መሳሪያዎችን መግጠም፣ ዲዛይን መስራት፣

    • የወለል ንጣፎችን ማስተካከል ዋና ዋና ተግባሮች ይሆናሉ።

ጥቅል ግንባታ

    • በአለቱ ላይ ይሚደርስን አደጋ ለመከላከልና አለቱን ለመጠበቅ ጥልቅ የድንጋይ ላይ ምርምር

    • በቅርሱ ላይ ያለውን መጠለያ አይናወጤነት አና ጥንካሪ በማጥናት ፤ አማራጭ መጠለያና መዋቅሩ ምን መሆን እንደሚችል እንዲሁም መጠለያው  መጠለያ በሊላቸው ሌያደርስ የሚችለውን ጉዳት አጥንቶል (የአብያተክርስቲያኑን፤ ፕላን፤ ቁመት፤ የመዋቅር ይዝት ጭመር ተመራምሮል)

የዲጂታል አውደ ርዕይ

    • የፎቶግራፍና ቪድዮ ምስሎችን በመጠቀም ዘመናዊና ተለምዶአዊ ግብዓትን በማጣመር ሲኖግራፍ በተባለዉ የማስጎብኛ መላ በመታገዝ አካታች የሆነ ጥበባዊ ተጓዥ ዓውደ-ርዕይ ነው፡፡

    • በዓውደ-ርዕዩ ከስፍራው ታሪካዊ፣ አጠቃላይ የአካባቢው ሁኔታ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በማዋሃድ በምናብ መሄድ፡፡

    • የዲጂታል አውደ-ርዕዩ በላሊበላ፣ አዲስ አበባና ፈረንሳይ ይቀርባል፡፡




የፕሮጀክቱ 5 ክፍሎች

ይህንን አቀራረብ ያስሱ (የታከቀደው ፕሮግራም 2022)

 

ዝርዝር

ከ2013 ጀምሮ የላሊቤላ ቡድኖች ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከባድ ገደቦችን መወጣት አስፈልገዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ግጭት በየጊዜው ወደ ስፍራው እንዳይደርሱ እንቅፋት ሆነዋል። ለአደጋ የተጋለጡ የአካባቢው ማኅበረሰቦች ድጋፍ በመስጠት እና ለየት ባለ የአካባቢ ቡድን በመታመን ከሁኔታዎች ጋር መላመድ ችለናል።

 
  • መጋቢት 2021፡ የዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት መጀመር።

    በነሐሴና ታህሳስ 2021 መካከል፣ ላሊበላ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ነበረች። በዚህ ወቅት፣ ህብረተሰቡ በምግብ አቅርቦት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በውሃና በመብራት ችግር ተሰቃይቷል። በርካታ ወጣቶች ከተማዋን ለቀው ሸሸተዋል። የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴዎች ተቋርጠው ስልጠናዎች በአዲስ አበባ ተሰጥቷል።

  • የአስቸኳይ ጊዜ ጥገና ስራዎችን መጀመር።

    የኤልክትሪክ ስራ ኩባንያ በጨረታ መምረጥ።

  • የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ማስተርስ ተማሪዎች፣ በቅርስ አስተዳደር ሥልጠና መስጠት (ኅዳር 2021)።

  • ለስድስት የአርኪኦሎጂ ተማሪዎች የመሬት ቁፋሮ ስራና የመስክ ላይ ስልጠና መስጠት (ከመጋቢት-ሚያዝያ 2021)፣

    ለአርኪዮሎጂ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስልጠና መስጠት (ህዳር 2021)፣

    የማህበረሰብ አቀፍ አርኪኦሎጂ፤ ከሰራተኞችና ከባለድርሻ የማህበረሰቡ አካላት ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ መሰረት የቁፋሮው ቦታ ቀይት ተራራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

  • የላሊበላ ከተማ ታህሳስ 2021 ከጦርነት ቀጠና ነጻ ወጥቶል። ባለፉት 5 ወራት ህብረተሰቡ ከባድ የኑሮ ጫና ውስጥ ወድቆ ነበር ሲሆነ የዝላቂ ቅርስ አድን ፕሮጀክት ቀስ በቀስ ወደ ስራ እየገባ ይገኛል።

  • ለ20 የእደ-ጥበብ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት።

    የአስቸኳይ ጊዜ ቅርስ ጥገና ስራውን ማስቀጠል (መጋቢት 2022)፣

    በቅርስ ጥበቃ ተማሪዎች፣ በቅርስ ጥገና ቴክኒኮች ጽንሰ-ሀሳብ ላይ የሶስት ቋንቋ ሙዳየ-ቃላት (ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ) ማዘጋጀት (መጋቢት 2022) ።

    በኤሌክትሪክ ስራ ዘርጋታና ጥናት ላይ በድርጅ አዋጭ የሆነን ስራ ይሰራል።

  • የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ስራዎቹ ሲጠናቀቁ፣ የሥዕሎቹ ጥገና ስራዎች ይጀምራሉ።

    የጽሑፎችና የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ጥበቃና እሴት መጨመር ስራ ላይ ስልጠና መስጠት (ግንቦት 2022)።

  • ስለ ቅርስ አስተዳደር ጽንሰ-ሀሳብ የቅርስ አስተዳደር ተማሪዎች የሶስት ቋንቋ ሙዳየ ቃላት (ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና አማርኛ) ዝግጅት (መጋቢት 2022)።

    ለቅርስ አስተዳደር ተማሪዎች ስለ ቀይት ተራራ ፓነሎች ፅንሰ-ሀሳብ ስልጠና መስጠትና የቦታው መስተጋብራዊ ጉብኝት (ሰኔ 2022)።

  • አርኪኦሎጂካዊ ስራና የመስክ ስልጠና ለ6 ተማሪዎች መስጠት (ሚያዝያ-ግንቦት 2022)፣

    በአርኪኦሎጂ ጽንሰ-ሀሳብ ላይ በአርኪኦሎጂ ተማሪዎች የሚዘጋጅ የሶስት ቋንቋ ሙዳየ ቃላት (ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛ እና አማርኛ) (መጋቢት 2022)።

    ማህበረሰብ አቀፍ አርኪኦሎጂ፡ የቀይት ተራራ ፅንሰ-ሀሳብ፣ የቅርስ አስተዳደር ተማሪዎች መስተጋብራዊ ጉብኝት፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች።

    በላሊበላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ወጣቶች ዘላቂ የላሊበላ ክለብ ማቋቋም።

  • ለዲጂታል ማዕከሉ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ግዢ።

    በመረጃ ቴከኖሎጂ ባለሙያ በላሊበላ የተለየ የመረጃ ቋት ማዘጋጀት።

    ቀሳውስቱን በዲጂታይዜሽን ሥራ ማሰልጠን።

  • ስልጠና የወሰዱ፡ 80 ተማሪዎች በቅርስ ጥበቃና አስተዳደር፣

    20 የእደ-ጥበብ ባለሞያዎች በቅርስ ጥገናና ጥበቃ ስልጠና ወስደዋል።

  • የአርኪኦሎጂ ሠራተኞች፣ አናጺዎች፣ ጥበቃዎች፣ አስተባባሪዎች...

  • 50+ ዓለም አቀፍና ፈረንሣዊ ባለሙያዎች

 
  • ሁለት የተለያዩ ደረጃዎች- ከጥር እስከ ሐምሌ፣ በላሊበላ የነበረው የፀጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ነበር። ይህም የዘላቂ ላሊቤላ ቡድን ቡድን በፕሮጀክት አፈጻጸም ረገድ ጉልህ መሻሻል እንዲያደርግ አስችሎታል። ከነሐሴ እስከ ኅዳር ባለው ጊዜ ውስጥ በአካባቢው አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር ። በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ከተማዋ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ ጸጥታ የሰፈነባት ከመሆኑም በላይ በወታደራዊ አስተዳደር ሥር ነበረች። ይሁን እንጂ በዚህ አለመረጋጋት ወቅት የዘላቂ ላሊቤላ ቡድን እንቅስቃሴዎች ፈጽሞ አላቆሙም - በቦታው የነበሩት 31 የእጅ ባለሙያዎች ድንገተኛ እርዳታዎችንና የቦታውን ውብነት በተመለከተ ሥራቸውን ቀጥለዋል ። በአምስቱም ክፍሎች ውስጥ እድገት ተደርጓል ።

  • የቀሩት አንዳንድ ጣልቃ ገብነት ዎች ማሟላት, እንዲሁም ተጨማሪ ተዛማጅ ስራዎች እንደ መሬት አቀማመጥ, የመንገድ ግንባታ, ደረጃዎች መገጠም, እና የጎን ማስከበሪያ ግድግዳ, እና መድረክ, ወዘተ።

  • በአብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክና የመብራት ስርዓት ማስተካከያ በተመለከተ ከጉዳዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያ ምክክር፣ እቅድ እና የፀደቀ ሂደት።

  • የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አባላት፣ የኢ.ኤ.ኤች ሹማምንትና ተማሪዎች የቲኦሬቲካልና (ወይም) ተግባራዊ ስልጠናዎች -

    1. የቅርስ ጥበቃ ሂደት

    2. የብራና ጽሑፎች ጥበቃ

    3. የብራና ጽሑፎች እና የቅርስ ዳታቤዝ ዲጂታይዜሽን

    4. የማይዳሰሱ ብሄራዊ ቅርሶች

    ለስልጠና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና ዲጂታል መሳሪያዎች ግዢ እና የማጓጓዣ ስራ ።

  • አዲሽአዴ ድልድይ ላይ ያለው ስራ መቀጠል።

    በዘላቂላ ላሊበላ ፕሮጀክት ውስጥ ከሰለጠኑት ተማሪዎች መካከል ከአንዱ ጋር የአርኪዮሎጂ ስራ ማከናወን።

  • የላሊቤላ 3D ኤግዚብሽን ‘እምነትን መቀረጽ’።

    የ"ቱኩል" ሙዚየም ግንባታ (ከአካባቢ ድንጋይእና እንጨት የተሠራ) እና ኤግዚቢሽኑ ወደዚህ ቦታ የመዘዋወር ስራ።

    በአካባቢው ከሚገኝ አንጥረኛ ጋር በመሆን ለቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ መብራት ከብረት የተሠራ ሽክርክሪት መሥራት።

 
 



ቡድኑ

  • የፕሮጀክት ቡድን መሪ

    የትውልድ ቦታ፡- ላሊበላ

    ትምህርት ዝግጅት፡- ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች አስተዳደር፣ የኢንዱስትሪ ቅርሶች ጥበቃና አስተዳደር፣የማስተርስ ዲግሪ ከፓሪስ ፓንቲዩን ሶርቦን ዩኒቨርስቲ፣ የተለያዩ ኮርሶች በፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ፖርቱጋልና ስፔን ተከታትሏል፡፡

    የስራ ልምድ፡- 12 ዓመታት በላሊበላ የባህል ልማትና አርኪኦሎጂ ሥራ፣ 2 ዓመት የላሊበላ የባህል ማዕከል ዳይሬክተርና መስራችነት፡፡

  • ሳይንሳዊ አስተባባሪ

    በብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከል የምርምር ዳይሬክተር፣ የመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ ልዩ የታሪክ ተመራማሪ። ከ2010 እስከ 2018፣ ተባባሪ ዳይሬክተር፣ ከ2019 ጀምሮ፣ የላሊበላ ታሪካዊና አርኪኦሎጂ (የጥንተ-ህንጻ ጥናት) ተልዕኮ ዳይሬክተር።

  • ሳይንሳዊ አስተባባሪ

    የማህበራዊ ሥነ መልከአ-ምድር ባለሙያ፣ ከ2018 ጀምሮ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር። የፒኤችዲ መመረቂያ ጽሁፍ፣ "ላሊበላ፣ በግሎባላይዜሽን ውስጥ የምትገኝ የኢትዮጵያ ከተማ"።

    በፓሪስ ናንቴር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፡፡

 
  • ረዳት አስተዳደር

    በሂሳብ አያያዝና አመራር ተመራቂ። ለዘላቂው የላሊበላ ፕሮጀክት አስተዳደርና ፋይናንስ ረዳት አስተዳደር።

  • የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ

    ከ 2013 ጀምሮ የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የበጀት አስተዳዳርና የሒሳብ ሥራ አስኪያጅ። ፕሮጀክቱን በስኬት እንዲመሩ፣ የበጀት አስተዳደር፣ የፋይናንስ ሪፖርቶች፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ ሆነዋል።

  • የአስቸኳይ ጥገና መርሀ-ግብር ኃላፊ

    ድንጋይ ጠራቢና የድንጋ ጥገና ባለሙያ፣ በብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከል ረዳት መሐንዲስ ። አሥራ ስድስት ዓመታት የአናስቲሎሲስ (የፈረሱ ሕንፃዎችንና ቅርሶችን እንደገና ጥገና) ኃላፊ ሆኖ በግብፅ ካርናክ ቤተመቅደሶች ላይ የሰራ። ለአሥር ዓመታት ያህል በ“ላሊበላ፣ ውቅር አርኪኦሎጂ” ስራ አባል።

 
  • የፍራንኮ-ኢትዮጵያ አርኪኦሎጂ ቁፋሮ ኃላፊ

    የአርኪዮሎጂና የጂኦ-አርኪሎጂ ባለሙያ። የTRACES ቤተ-ሙከራ (ቱሉዝ) እና የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል (የብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከል) ውስጥ ይሰራሉ። ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በላሊበላ የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ ኃላፊ።

  • በማኔጅመንት እና በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ተመራቂ። ዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት አስተዳደር እና ፋይናንስ ረዳት (ጊዜያዊ ምትክ)።

  • የላሊበላ አብያተ ቤተክርስቲያን የፍራንኮ-ኢትዮጵያ ትብብር ፕሮግራም ቃል አቀባይ/አስተባባሪ።

    የትውልድ ቦታ፡- ላሊበላ። የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ።

  • የዶክትሬት ዲግሪ (2007) በፈረንሳይ የባሕል ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኝ የጥበቃ ሳይንቲስት ናችው። የላሊቤላን ሥዕሎች ከማጥናት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ለሥነ-ሥርዓትና ለአርኪዮሎጂያዊ እቃዎች ጥበቃ የሚሰለጥኑትን ሥልጠና በበላይነት ይከታተላል።

 



የፕሮጀክቱ አስተናጋጅ ተቋም

የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል

የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል (CFEE) UAR3137 የፈረንሳይ የአውሮጳና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (MEAE) እና ብሔራዊ የሳይንስ ምርምር ማዕከል (CNRS / INSHS) የውጭ ሀገር የፈረንሣይ የምርምር ተቋም (IFRE) የጋራ ዩኒት ነው። በአዲስ አበባ የተመሰረተ ነው። ወደ አንድ መቶ ዓመት የሚጠጋ የፍራንኮ-ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ትብብር ወራሽ ነው።

የ CFEE እንቅስቃሴዎች የምድር ሳይንስ, ፓሊዮቶሎጂ, አርኪኦሎጂ, ሰብአዊነት እና ማህበራዊ ሳይንስ, እንዲሁም የአካባቢ ሳይንስ መስኮች ጋር ያያይዙ. በቅርስ ዘርፍም ሳይንሳዊ ድጋፍ ያደርጋል (Sustainable Lalibela - ዘላቂ ላሊበላ, National Palace - ቤተ መንግሥት, National Museum of Ethiopia - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም)።

ዣን-ኒኮላ ባክ, ዳይሬክተር

ማሪ ብሪዶኖ, የቀድሞ ዳይሬክተር

 



አጋሮች

ብሄራዊ ሳይንሳዊ ምርምር ማዕከል

የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል በተመራማሪዎቹ፣ በመሃንዲሶቹ (ኢንጂነሮቹ)፣ እና በቴክኒክ ባለሙያዎቹ በላሊበላ መሳተፍ ከጀመረ ከአስር አመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ማዕከሉ ይህን የላሊበላን-ማስቀጠል ፕሮጀክት በመደገፉ የሚሰማው ደስታ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ በፈረንሳይ እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ጥምር የምርምር ቡድን ተመራማሪዎቹ፣ መሃንዲሶቹ(ኢንጂነሮቹ)፣ እና የቴክኒክ ባለሙያዎቹ አማካኝነት በላሊበላ እየተሰራ ካለው ስራ በተጨማሪ፤ መጠነ ሰፊ የሆነ የሳይንሳዊ ምርምር ጥምረትን በፈረንሳይና ኢትዮጵያውያን ባልደረቦች መካከል በተቀናጀ መንገድ ጥምረት ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

የተለያዩ የፕሮጀክቱ ክፍል መሰረታዊ ምርምርን ያጣመረ፣ የተሳትፎ ምርምርን እና የምርምር ወቅት የሚደረግን ስልጠና ስፍራውን መጠበቅ እና መንከባከብ ዓላማ ያደረገ እንዲሁም የማዕከሉን ሳይንሳዊ እና አለምአቀፋዊ ፖሊሲ ከማሳካት አንፃር ነው፡፡ የምርምሩ ቃልኪዳን ቃለ ጉባኤ ከኢትዮጵያውያን የሳይንሳዊ እና የባህል ተቋም ባልደረቦች ጋር በመጣመር ሲሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ያማከለ የተቀናጀ የፅንሰ-ሃሳብ እና የተግባር ስልጠናን ያካተተ ነው፡፡ ይህንንም በዋናነት ወጥ የሆነ ችሎታን እና በሙያው የተካነን ባለሙያ ለማፍራት የሚያስችል ሲሆን በምርምር ሲታገዝ ደግሞ የማህበረሰቡንና የሃገሪቱን ፍላጎት በብቃት ለማሟላት ያስችላል፡፡

ሲልቪ ድሙርዥ

የምርምር ዳይሬክተር

 

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ እና በቴክኒክ ይደግፋል፡፡  በዚህም መሰረት ኤጀንሲው በህዳር 2020 ለዚህ አጓጊ እና የተቀናጀ የላሊበላን-ማስቀጠል ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ እንዲሆን ለCNRS የ3.3 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡  ይህ ፕሮጀክት የተቀረፀው የፌደራል፣ የክልሉ እንዲሁም የህያው ቅርሱ የበላይ ጠባቂዎች በተገኙበት ነው፡፡

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD)  በተለይ በበርካታ ፕሮጀክት አካላት ዙሪያ የሚያተኩር ሲሆን በትግበራ ትርጓሜዎች፣ በአፈፃፀም እና ሂደት ዙሪያ በኢትዮጵያውያንና ፈረንሳውያን ተወካዮች የሚደረጉ ተከታታይ ውይይቶችን ተግባራዊ ያደርጋል። የበርካታ ተቋማትን እና ተሳታፊዎች የዘላቂ ልማት ግንባታ እንዲፈጸም ያደርጋል። የሃገር በቀል ዕደ-ጥበብ ባለሙያ፣ የወደፊት አርኪዮሎጂ ሰልጣኞች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የቅርስ አስተዳዳር እውቀትና ችሎታቸውን ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛል። የኢትዮጵያ የቅርስ ስፍራዎች ፤ ለቦታው እንክብካቤ የሚያደርጉ የአካባቢው አስጎብኝዎች፤ ስለስፍራው ያለውን ግንዛቤ ያሳድጋል። የመረጃ ቋት ግንባታ ሂደት ውስጥ የማህበረሰብ እና የተለያዩ ህዝባዊ ተሳትፎዎች  በፕሮጀክቱ እንዲካተቱ ድጋፍ ያደርጋል፡፡    የፈረንሳይ ልማት ወኪል ኤጀንሲ (AFD) ለኢትዮጵያ መንግስት የድጋፍ እንቅስቃሴውን የጀመረው እ.ኤ.አ ከ1996 ጀምሮ ነው፡፡ ይህም የህዝባዊ ተቋማትን እና የሲቪል ማህበረሰቡ  በተለያየ ዘርፍ  እንደ ውሃ፣ ሐይል ዝርጋታ፣  የገጠር ልማት እና ግብርና ላይ የሚሳተፍ ሲሆን ይህም በአጠቅቃላይ  ከ600 ሚ ዩሮ በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ሉዊ-አንትዋን ሱሼ, ዳይሬክተር

ቫለሪ ቴሂዮ, የቀድሞ ዳይሬክተር

 

የፈረንሳይ ኤምባሲ

በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ሂደት ውስጥ ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት አስመስክራለች፡፡ ከፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን እና ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወዳጅነት  የረጅም ጊዜ የነበረንን  የባህል ግንኙነት በማንቃቱ፤ ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ ተመራማሪዎችን ግንኙነት ዳግም አነሳስቷል፡፡ 

ዛሬ ይህንን ታሪክ ይዘን ነው  የላሊበላ የቅርስ ጥበቃና ጥገና ፕሮግራም ላይ ያለነው፡፡ በዚህም መሰረት የሳይንሳዊ ምርምርና ስልጠናዎችን ለቅርሶቹ የደህንነት ጠባቂዎች ኢትዮጵያውያን ተዋናዮች ይህንኑ ታሪክ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ጥምር ምኞታችንን ለመፍጠርም፣ ፕሮጀክቱ የሳይንሳዊ አቀራረብንና የመቀራርብ ወዳጅነትን ከላሊበላ ነዋሪዎችና ከወኪሎቻችው ጋር አስምሯል፡፡ በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥም ፈረንሳይ ለገባችዉ ቃል በታማኝነት ፀንታ ትቆማለች፡፡ ይህም የምናምንበትን ማሳየት ቀጣዩ ትውልድ በእነዚህ ቅርሶች ጥላ ስር ማደጉን ማረጋገጥ በሂደት የሚያስተላልፉት ትውስታ ነው፡፡ ምክኒንያቱም ቅርስ ለፖለቲካዊ ህብረት  ፣ለትውልድ ጥምረት ፣ለፅኑ ትውልድ መፍጠር፣ ለግዛት አንድነትና ለህዝቦች እኩልነት የሚያደርገው አስተዋፅ ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ 

ይሄን ስራ በታላቅ ስኬት እየመራ ላለው የፈረንሳይ የኢትዮፕጵያ ጥናት ማዕከል እና ለብሄራዊ ሳይንሳዊ ምርምር ማዕከል (CNRS) ቡድን አባላት እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን ባልደረቦቻቸው ጋር በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) ድጋፍ በማድረግ እና በመተግበር ስላከናወኑት ስራ ለማመስገን እወዳለሁ፡፡

ሬሚ ማሬሾ

በኢትዮጵያና አፍሪካ ህብረት የፈረንሳይ አምባሳደር

 

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን

የላሊበላ ደብር ጽህፈት ቤት አስተዳደር  በአለም-አቀፍ እና በዘርፈ-ብዙ ባለሙያዎች የሚመራውን የፈረንሳይ ኢትዮጵያን የላሊበላን-ማስቀጠል ቡድን ይህንን የዓለም ቅርስ የሆነውንና ለኛ ኩራት ከመሆን በላይ የህይወታችን መድህን የሆነውን ውቅር አብያተ-ክርስቲያን ለማደስ፣ ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ ዓላማ አድርጋችሁ ስለመጣችሁ የተሰማኝን ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡ በስራችሁ ሁሉ ከጎን ሆነን የምናግዝ ሲሆን እናንተም ለተሰጣችሁ ተግባር የታመናችሁና የተጋችሁ ትሆኑ ዘንድ አደራ እንላለን።

አባ ሂርያቆስ, ቅዱስ ላሊበላ ደብር ጽ/ቤት

መምህር ቆሞስ ጽጌስላሴ መዝገቡ, የቀድሞ

 

ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ፣ ማጎልበትና ምርምር በበላይነት የሚሰራው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ባለስልጣን ነው። በተጨማሪም ዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታዎችን በአግባቡ የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት ። በዚህም የዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት ግንባር ቀደም አጋር ነው።

አበባው አያሌው, ዳይሬክተር